1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዶይቸ ቬለን ያድምጡ

የዕለቱን ዝግጅት ለማዳመጥ 16:00 - 17:00 የሚለውን ማገናኛ ይጫኑ። የአንድ ሣምንቱ የስርጭት ኮሮጆም "ዝግጅት"ን በመጫን ሊገኝ ይችላል። የአማርኛ፣ የኪስዋሂሊ፣ የሀውሳ፣የእንግሊዝኛ፣ የፈረንሣይኛ እና የፖርቱጊዝኛ ቋንቋ ሥርጭትን በሚተላለፍበት ጊዜ በኢንተርኔት በቀጥታ ማድመጥም ይቻላል።

አስተያየታችሁ ዓቢይ ግምት የሚሰጠው ነው፤ በ +49-228-429-164995 ደውሉልን። በዕለቱ ዓቢይ ርዕስ ላይ በ+49 172 26 66 944 በSMS አስተያየት ላኩልን። ባጠቃላይ በዝግጅታችን ላይ አስተያየታችሁን በኢሜይልም ልትልኩልን ትችላላችሁ።

amharic@dw.de



  • ደቡብ አፍሪቃ....

    የአፍሪቃ ዋንጫ ፍጻሜ 2013

    ደቡብ አፍሪቃ....

    በጎርጎሮሳውያኑ 2013 የሚካሄደው የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ ፍጻሜ ውድድር የምድቦች ዕጣ በጥቅምት አጋማሽ ደርባን ላይ ወጥቷል። 16 ቡድኖች በፊታችን ጥርና የካቲት የዋንጫ ባለቤት ለመሆን ሲታገሉ ይከርማሉ።

  • አይቮሪ ኮስት ሁለተኛነት በቅቷታል

    የአፍሪቃ ዋንጫ ፍጻሜ 2013

    አይቮሪ ኮስት ሁለተኛነት በቅቷታል

    በዝሆኖች የሚመሰሉት የአይቮሪ ኮስት ተጫዋቾች ወደ ደቡብ አፍሪቃ የሚያመሩት የሁለተኝነት ማዕረጋቸውን ይዘው ነው። በማጣሪያው ሤኔጋልን አሸንፈዋል። አይቮሪ ኮስት በመጀመሪው ግጥሚያ አቢጃን ላይ 4-2 ስታሸንፍ የመልሱ ጨዋታ ዳካር ላይ አይቮሪ ኮስት 2-0 እየመራች ሳለ በኹከት ሳቢያ መቋረጥ ነበረበት። በዚሁም ሤኔጋል ልትታገድና አይቮሪ ኮስት ልታልፍ በቅታለች። በምድብ-አራት ውስጥ ተጋጣሚዎቿ ቱኒዚያ፣ አልጄሪያና ቶጎ ይሆናሉ።

  • ኢትዮጵያ የሚጠብቃት ፈተና

    የአፍሪቃ ዋንጫ ፍጻሜ 2013

    ኢትዮጵያ የሚጠብቃት ፈተና

    የብሄራዊ ቡድኑ አሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው ቡድኑን ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ባደረጉት ጥረት ለፍጻሜ ዙር ለማድረስ በቅተዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪቃ ዋንጫ ፍጻሜ ሳትሳተፍ እስካሁን 31 ዓመታት ነው ያሳለፈችው። በ 1962 እንደ አስተናጋጅ አገር የሶሥተኛው የአፍሪቃ ዋንጫ ባለቤት ለመሆን መብቃቷ የእስከዛሬ መኩሪያዋ ነው። ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በምድብ-ሶሥት ውስጥ ያለፈው ዋንጫ ባለቤት ዛምቢያ፣ ናይጄሪያና ቡርኪና ፋሶ ይጠብቋታል። ከባድ ምድብ ነው የገጠማት።

  • ያለፈው ዋንጫ ባለቤት ዛምቢያ

    የአፍሪቃ ዋንጫ ፍጻሜ 2013

    ያለፈው ዋንጫ ባለቤት ዛምቢያ

    የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን በ 2012 የአፍሪቃ ዋንጫ ውድድር ያገኘው ድል በአጭሩ የሚረሣ አይደለም። ዛምቢያ በፍጻሜው ጨዋታ ከጭማሪ ሰዓት በኋላም ባልለየለት ግጥሚያ አይቮሪ ኮስትን በፍጹም ቅጣት ምት 8-7 አሸንፋ ነበር ለሁለተኛ ጊዜ የዋንጫ ባለቤት ለመሆን የበቃችው። ቡድኑ በመጪው የ 2013 የአፍሪቃ ዋንጫ ፍጻሜ ውድድር በምድብ-ሶሥት ውስጥ የናይጄሪያ፤ የቡርኪና ፋሶና የኢትዮጵያ ተፎካካሪ ነው።

  • የጋና ሕልም አምሥተኛ ዋንጫ ነው

    የአፍሪቃ ዋንጫ ፍጻሜ 2013

    የጋና ሕልም አምሥተኛ ዋንጫ ነው

    ጋና እስካሁን አራት ጊዜ የአፍሪቃን ዋንጫ አግኝታለች። ስምንት ጊዜ ለፍጻሜ የደረሰችም አገር ናት። ለመጨረሻ ጊዜ ከሁለት ዓመት በፊት አንጎላ ውስጥ ለፍጻሜ ስትደርስ በጥቂቱ በግብጽ 1-0 መረታቷ ይታወሳል። ታዋቂ ተጫዋቿ በስተቀኝ የሚታየው የኦላምፒክ ማርሤይ የመሃል ሜዳ ኮከብ አንድሬ አየው ነው። ጋና በምድብ-ሁለት ውስጥ ከማሊ፣ ከኒጀርና ከዴሞክራቲክ ሬፑብሊክ ኮንጎ በአንድ ተደልድላለች።

  • ናይጄሪያ ከቀደምቱ አንዷ ናት

    የአፍሪቃ ዋንጫ ፍጻሜ 2013

    ናይጄሪያ ከቀደምቱ አንዷ ናት

    የናይጄሪያ ብሄራዊ ቡድን አፍሪቃ ውስጥ ግሩም ከሚባሉት አንዱ ነው። ናይጄሪያ በ 1994 በዓለም የእግር ኳስ ፌደሬሺኖች ማሕበር በፊፋ የማዕረግ ተዋረድ ላይ አምሥተኛውን ቦታ ለመያዝ በቅታ ነበር። ይህ ደግሞ እስካሁን አንድም የአፍሪቃ አገር ያልደረሰበት ደረጃ ነው። አገሪቱ በ 1980 እና 1994 የአፍሪቃን ዋንጫ አሸንፋለች። ሶሥት ጊዜም ሶሥተኛ ነበረች። ናይጄሪያ የተሰለፈችው በምድብ-ሶሥት ከዛምቢያ፣ ከኢትዮጵያና ከቡርኪና ፋሶ ጋር ነው።

  • ቡርኪና ፋሶ ጥሩ ውጤት ትመኛለች

    የአፍሪቃ ዋንጫ ፍጻሜ 2013

    ቡርኪና ፋሶ ጥሩ ውጤት ትመኛለች

    ምዕራብ አፍሪቃይቱ አገር ታላቅ የእግር ኳስ ታሪክ የላትም። የእስካሁን ከፍተኛ ውጤቷ በ 1998 የአፍሪቃ ዋንጫ ፍጻሜ ለአራተኛ ቦታ መብቃቷ ነው። ከዚያን ወዲህ እርግጥ ያለማቋረጥ ለፍጻሜ ዙር መድረሱ ሲሳካላት ቆይቷል። ኮከብ ተጫዋቿ አጥቂዋ ሞሙኒ ዳጋኖ ሲሆን በምድብ-ሶሥት ዛምቢያ፣ ናይጄሪያና ኢትዮጵያ ይጠብቋታል።


    አዘጋጅ: መሥፍን መኮንን | ዋና አዘጋጅ: ሂሩት መለሰ

አስተያየትዎ