1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
Wer hat das Bild gemacht?: Das Bild wurde durch die Künstlerin gestellt. 
Wann wurde das Bild gemacht?: Eingestellt Oktober 2012
Wo wurde das Bild aufgenommen?: Äthiopien
Bildbeschreibung: Spielende Kinder in Addis Abeba in Verein von Let me be a child e.V. 
Etagegne Girma-Bierig und Absolventen.

ባሕል እና ወጣቶች

ህፃናት ህፃን ሆነው ሲያድጉ

ወ/ሮ እታገኝ ግርማ ቢርግ በጀርመን ሀገር LET ME BE A CHILD የሚባል ማህበር ካቋቋሙ አስር አመት ሊሆናቸው ነው። ማህበሩ ኢትዮጵያ ውስጥ የተቸገሩ ህፃናት እና ወጣቶችን ይረዳል።

ማህበሩ በአዲስ አበባ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ከሆሳና ግማሽ ሰዓት ርቀት ላይ በምትገኝ ዶዮገና ከተማ በጠቅላላው 100 ልጆችን ይረዳል። ለልጆቹ ለትምህርት ቤት የሚያስፈልጋቸውን መሳሪያ ማቅረብ፤ የተመጣጠነ ምግብ መስጠት እና ጥናት ማስጠናት ከድጋፎቹ ጥቂቶቹ ናቸው።

Wer hat das Bild gemacht?: Das Bild wurde durch die Künstlerin gestellt. 
Wann wurde das Bild gemacht?: Eingestellt Oktober 2012
Wo wurde das Bild aufgenommen?: Äthiopien
Bildbeschreibung: Spielende Kinder in Addis Abeba in Verein von Let me be a child e.V. 
Etagegne Girma-Bierig und Absolventen. 
ወ/ሮ እታገኝ እና ድጋፍ ሲያደርጉላቸው የቆዩት ወጣቶች

ስንጀምር በወር 500€ ብቻ ነበር የምንልከው ዛሬ በጠቅላላው 3600€ ያስፈልገናል ይላሉ ወ/ሮ እታገኝ፤ ። ይበልጡ ግን የሚፈፀመው በፍቃደንነት በነፃ በሚያገለግሉ ሰዎች ነው። ከነዚህም አንዷ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ የምትገኘው ካተሪና ሉዊስ ናት። ወጣቷ ከግማሽ አመት በፊት በስዕነ አዕምሮ ተመርቃለች። በ LET ME BE A CHILD ስላላት የስራ ድርሻ እንዲህ ትላለች።
« በአሁኑ ሰዓት መጽሀፍ ቤት እያደራጀን እንገኛለን። አዳዲስ መጽሀፍ ለልጆቹ ገዝተናል። ይህንን እያሰባሰብኩ እገኛለሁ። ልጆች መፅሀፍ የሚዋሱበትን መንገድ እያሰባሰብኩ ነው። ሌሎች ስራዎችም አሉኝ። ወላጆች ልጆቻቸውን ሀኪም ቤት ለመውሰድ ካልተመቻቸው ከባልደረቦቼ ጋ በመሆን ይዘናቸው እንሄዳለን። አንድን ልጅ ኮሌጅ አስመዝግበናል። ት/ቤታቸውን እጎበኛለሁ። የህፃናቱንም ወላጆች ለመጠየቅ ከባልደረቦቼ በመሆንም እሄዳለሁ።»

Wer hat das Bild gemacht?: Das Bild wurde durch die Künstlerin gestellt. 
Wann wurde das Bild gemacht?: Eingestellt Oktober 2012
Wo wurde das Bild aufgenommen?: Äthiopien
Bildbeschreibung: Spielende Kinder in Addis Abeba in Verein von Let me be a child e.V. 
Etagegne Girma-Bierig und Absolventen. 
ማህበሩ በጠቅላላው 100 ልጆችን ይረዳል

ካተሪና ከ ሁለት ወር በላይ አዲስ አበባ ውስጥ ትቆያለች። ጥሩ ልምድ ነው እየቀሰምኩ ያለሁት ትላለች። «ከማውቀው አህጉር የተለየ ባህል ነው እዚህ ያለው። እንደዚህ አይነት ሀገር ተሄዶ ሰው ሲረዳም ለራስ ብዙ ነገር መቅሰም ይቻላል። ለምሳሌ አሲስ ባህልን መተዋወቅ። ለኔ እስካሁን የአፍሪቃ ባህል እንግዳ ነበር። ብዙ ቀለማት ያሉት ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ምግቡ ይጣፍጣል። ሰዎቹ ፈገግተኞች ናቸው። እንደ ጀርመን ሀብታም ያልሆነ ሀገር ኖሮ ማየቱም ጥሩ ልምድ ነው።»

አንድነት አባቡ፤ ዛሬ 19 አመቱ ነው። በዚህ ድርጅት ታቅፎ ቆይቷል። በዚህ አመት ጀምሮ በአልሙኒየም ድርጅት ውስጥ ቴክኒሺያን ሆኖ ያገለግላል። ዛሬ ለደረሰበት ቦታ ይህ ማህበር ትልቅ አስተዋፅሳኦ አድርጎልኛል ይላል።

በጀርመን ሀገር የ LET ME BE A CHILD ማህበር መስራች እና የቦርድ ሊቀመንበር፣ ወ/ሮ እታገኝ ግርማ ቢርግ፤ ማህበሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ድጋፍ ያደረገለት ወጣት፤ አንድነት አባቡ እና በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ ውስጥ ለዚሁ ማህበር በፍቃደኝነት የምታገለግል ጀርመናዊት ካተሪና ሊዊስ ያጫወቱንን ከወጣቶች አለም የድምፅ ዘገባ ያገኙታል።

ልደት አበበ
ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic