1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዶይቸ ቬለን ያድምጡ

የዕለቱን ዝግጅት ለማዳመጥ 16:00 - 17:00 የሚለውን ማገናኛ ይጫኑ። የአንድ ሣምንቱ የስርጭት ኮሮጆም "ዝግጅት"ን በመጫን ሊገኝ ይችላል። የአማርኛ፣ የኪስዋሂሊ፣ የሀውሳ፣የእንግሊዝኛ፣ የፈረንሣይኛ እና የፖርቱጊዝኛ ቋንቋ ሥርጭትን በሚተላለፍበት ጊዜ በኢንተርኔት በቀጥታ ማድመጥም ይቻላል።

አስተያየታችሁ ዓቢይ ግምት የሚሰጠው ነው፤ በ +49-228-429-164995 ደውሉልን። በዕለቱ ዓቢይ ርዕስ ላይ በ+49 172 26 66 944 በSMS አስተያየት ላኩልን። ባጠቃላይ በዝግጅታችን ላይ አስተያየታችሁን በኢሜይልም ልትልኩልን ትችላላችሁ።

amharic@dw.de



  • እአአ ጥቅምት 9፣ 1962

    የዮጋንዳ 50ኛ የነፃነት አመት

    እአአ ጥቅምት 9፣ 1962

    …ዮጋንዳ ከ 66 ዓመት የብሪታንያ ቀኝ ግዛት በኃላ ነፃ ወጣች። ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ ስልጣኑን ከአገረ ገዢ ዎልተር ካውትስ ተረከቡ። በወቅቱ ብሪታንያን ወክለው የተገኙት ኸርዞጊን እና ኸርዞግ ኬንት ነበሩ።

  • ሚልተን ኦቦቴ

    የዮጋንዳ 50ኛ የነፃነት አመት

    ሚልተን ኦቦቴ

    ...የንጉሰ ነገስታትን ስርዓት አስወገዱ። ሚልተን ኦቦቴ ከ 1966 አንስተው እአአ ጥር 25፣ 1971 የጦር መሪ ኢዲ አሚን ከስልጣን እስኪያስወግዷቸው ድረስ በፕሬዚዳንት ቆይተዋል። ኦቦቴ ምርጫ በማጭበርበር እአአ 1980 መልሰው ስልጣን ጨበጡ። ሁለተኛ የስልጣን ዘመናቸው ጭቆና የበዛበት፣ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች የሞቱበት እና የተሰደዱበት ነበር።

  • ኢዲ አሚን

    የዮጋንዳ 50ኛ የነፃነት አመት

    ኢዲ አሚን

    …እአአ ከ1971 ዓ ም እስከ 1979 ዓ ም በቆየው ጨካኝ አመራራቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ታስረዋል፣ ተደብድበዋል፣ እንዲሁም ተገድለዋል። ተቃዋሚዎችን ለአዞ መግበዋል። ሰዎች እርስ በርስ በመዶሻ እንዲፈላለጡም አድርገዋል። እስያውያን ንብረታቸው ተነጥቀዋል፣ በሺ የሚቆጠሩም ከሀገር ተባረዋል። በመጨረሻም፣ ኢዲ አሚን ተገን በጠየቁባት ሳውዲ አረቢያ እአአ 2003 ዓ ም አረፉ።

  • የዩጋንዳ ነፃ አወጣጥ

    የዮጋንዳ 50ኛ የነፃነት አመት

    የዩጋንዳ ነፃ አወጣጥ

    እአአ 1979 ዓም ጎረቤት ሀገር ታንዛንያ ለዩጋንዳ ከፍተኛ ድጋፍ አድርጋለች። የታንዛንያ ወታደሮች በውጪ ሀገር ተገን ከጠየቁት የዩጋንዳ ዜጎች ጋ ባንድነት በመሆን አምባ ገነን መሪ የኢዲ አሚን የስምንት ዓመት የችካኔ አገዛዝ አብቅተዋል። እአአ 1980 ሚልተን ኦቤቱ መልሰው ስልጣን ጨበጡ። ዮዌሪ ሙሴቬኒ ከ 1986 ስልጣኑን ያዙ፣ እስካሁንም የዮጋንዳ ፕሬዚዳንት ናቸው።

  • የአፍሪቃ ሉል

    የዮጋንዳ 50ኛ የነፃነት አመት

    የአፍሪቃ ሉል

    ሲሉ ነበር የቀድሞው የብሪታንያ ጠ/ሚኒስትር ዊንስትን ቸርችል ምስራቅ አፍሪቃዊቷን ሀገር የጠሯት። ለም፣ አረንጓዴ እና በሀይቅ የተከበበ መሬቷ፣ ጫካ እና ተራራው ይማርካቸው ነበር። በምድር ወገብ ያለው የአየር ንብረት ለሙዝ ፣ ሸንኮራ አገዳ እና ለጥጥ ምርት ተስማሚ ነው። በተለይ ወደውጭ በንግድ የሚላክ ቡና ታመርታለች።

  • ጆሴፍ ኮኒ

    የዮጋንዳ 50ኛ የነፃነት አመት

    ጆሴፍ ኮኒ

    …እስካሁን ድረስ በጥብቅ የሚፈለጉ የጦር ወንጀለኛ ናቸው። ራሱን Lord Resistance Army (LRA) ብሎ የሚጠራው ያማፅያን ቡድን ከ20 አመታት በላይ በሰሜን ዮጋንዳ ህዝቡን አሸብረዋል። ሁለት ሚሊዮን የሚጠጋ ሰውም የዚሁ ሽብር ሰለባ ሆኖዋል። LRA በግዳጅ 20 000 ህፃናትን ለውትድርና መልምሏል። የሰላም ስምምነቱ ሳይሳካ በመቅረቱም እአአ ከ2008 አንስቶ በጎረቤት ዴሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ እና መካከለኛው ኮንጎ ሽብሩን ቀጥሏል።

  • ኪዛ ቤሲጄይ

    የዮጋንዳ 50ኛ የነፃነት አመት

    ኪዛ ቤሲጄይ

    …የተቃዋሚዎች መሪ እና የዲሞክራሲ ለውጥ ግንባር (FDC) ሊቀመንበር በተደጋጋሚ በምርጫ ተሸንፈዋል። ቤሲጄይ በመርሃ ግብራቸው ህዝቡን ለማሳመንም ሆነ የተቃዋሚዎች አልቻሉም። ከ 2011 ዓ ም አንስቶ ወደስራ ቦታህ በእግርህ ተጓዝ የተሰኘ ዘመቻ በመጀመር፣ በምግብ ዋጋ ንረት እና በማህበረሰቡ በሚታየው ማህበራዊ ኢፍትሃዊ ሁኔታዎች ተቃውሞ ያሰማሉ።

  • ጭቆና

    የዮጋንዳ 50ኛ የነፃነት አመት

    ጭቆና

    የተቃውሞ ሰልፎች አብዛኛውን ጊዜ በፀጥታ ኃይሎች ጉልበት የተሞላበት ርምጃ እና አፈሳ ይደመሰሳሉ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ፖሊስ እና የምክር ቤት አባላት በሰው ላይ ለሚያደርሱት በደል ለፍርድ አይቀርቡም ሲሉ ይወቅሳሉ።

  • የግብረ ሶዶማዊነት ጥላቻ

    የዮጋንዳ 50ኛ የነፃነት አመት

    የግብረ ሶዶማዊነት ጥላቻ

    ግብረ ሶዶማዊነት ዮጋንዳ ውስጥ ተስፋፍቶ ይገኛል። በ2010 አንድ ጋዜጣ የግብረ ሶዶማውያንን ስም እና አድራሻ የያዘ እትም ካወጣ በኋላ በሀገሪቷ ትልቅ አሰሳ ተካሂዶ ነበር። ዮጋንዳ ግብረ ሶዶማዊነትን የሚከለክል ህግ አላት። ይህንንም ዮ ኤስ አሜሪካ እና አውሮፓ በጥብቅ ያወግዛሉ።

  • የሰላም አስከባሪ ኃይላት

    የዮጋንዳ 50ኛ የነፃነት አመት

    የሰላም አስከባሪ ኃይላት

    ላለፉት አመታት የዮጋንዳ ጦር ኃይላት በሶማሊያ ሰላም ለማስከበር ከሶማሊያ የሽግግር መንግስት ጎን በመሰለፍ እየታገሉ ይገኛል። በሶማሊያ የአፍሪቃ ህብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል(AMISOM) ወደ ሶማሊያ ከላካቸው ወታደሮች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት ዮጋንዳውያን ናቸው። በዚህም የተነሳ ዮጋንዳ በተደጋጋሚ የአሸባብ ኢላማ ሆናለች።

  • የ 2011ዱ ምርጫ

    የዮጋንዳ 50ኛ የነፃነት አመት

    የ 2011ዱ ምርጫ

    «ነፃ ግን ትክክለኛአልነበረም። ነበር የምርጫ ታዛቢዎች አስተያየት። የዮጋንዳ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ለመራጮች ያቀረቡት ስጦታ እና ገዢው የNRM ፓርቲ በመንግስት ወጪ የሸፈነው ውዱ የምርጫ ዘመቻ ፓርቲው ላሸነፈበት ድርጊት ሚና ተጫውቷል። እአአ 2005 ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በተወዳዳሪነት መቅረብ እንዲችሉ ህገ መንግስቱን ቀይረዋል።

  • አገር ጎብኚዎች

    የዮጋንዳ 50ኛ የነፃነት አመት

    አገር ጎብኚዎች

    የነጭ አባይ ምንጭ መሆንዋ ፣ ተራራማው የመሬት አቀማመጥዋ እና ጫካዎቿ ዮጋንዳን የአገር ጎብኚዎች አተወዳጅ የዕረፍት ቦታ ድርጓታል። ዝንጀሮዎች እና ስጋት የተደቀነባቸውን ገመሬ ዝንጀሮዎችን መመልከት ይቻላል። ዮጋንዳ ከ 2012 ጀምሮ « ብቸኛ ፕላኔት» በተሰኘው የሀገራት ማወዳደሪያ መዘርዝር ላይ ሰፍራለች።

  • ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ

    የዮጋንዳ 50ኛ የነፃነት አመት

    ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ

    ባንድ ወቅት ብዙ ዓመታት በስልጣን የሚቆዩ የአፍሪቃ ርዕሳነ ብሔር ከሚተቹ ሀያስያን መካከል አንዱ የነበሩት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ዛሬ ራሳቸው የዕድሜ ልክ ፕሬዚዳንት ሆነው መቆየት ይፈልጋሉ። ይህ ከሳቸው ሌላ ፕሬዚዳንት አይቶ ለማያውቀው ወጣት የሀገሪቱ ሕዝብ አስደንጋጭ ሆኖዋል። ሙሴቬኒ ካለፉት 26 አመታት ወዲህ በስልጣን ላይ ይገኛሉ።


    አዘጋጅ: ልደት አበበ | ዋና አዘጋጅ: አርያም ተክሌ

አስተያየትዎ