እሥራኤል በደቡብ ካርቱም የሚገኘውን የሱዳን የያርሙክ የጦር መሣሪያ ፋብሪካን በሚሳይል ደብድባለች ሲል የሱዳን መንግሥት ወቀሳ ሰነዘረ። ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ በአንድ ጊዜ በአራት ተዋጊ አይሮፕላኖች በተካሄደው ጥቃት ሁለት የፋብሪካው ሰራተኞች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸውን ሱዳን ገልጻለች።
በአብዛኛዉ በዩናይትድ ስቴትስ የዉጪ መርሕ ላይ ባተኮረዉ ክርክር ፕሬዝዳት ኦባማ የአራት አመት የመሪነት ልምዳቸዉን በትክክል ማንፀባረቅ መቻላቸዉን ክርክሩን የተከታተሉ ታዛቢዎች አረጋግጠዉላቸዋል።
ሁሉምበየተቃዋሚዎቻቸዉ ሲሸነፉ ግን ሥልጣን ሐገራቸዉን አንድም ለየአሸናፊዎቻዉ እየጣሉ ተሰደዱ፣ ሁለትም እየተማረኩ ታሰሩ፣ ሰወስትም የፍርዱ ሒደት ምንም ይሁን ምን እየተፈረደባቸዉ ተገደሉ እንጂ ጦር ሜዳ፥ ቆስለዉ፥ ተማርከዉ ያልፍርድ አልተገደሉም።
በመኪና በተጠመደ ፈንጂ ከተገደሉት ከፍተኛ የደህንነት መስሪያ ቤት ባለስልጣን ዊሳም አል-ሃሳን የቀብር ስነ-ስርዓት በኋላ የሊባኖስ መዲና ቤሩት ግጭት ተስፋፍቶባታል። ትናንት ማምሻዉን ዛሬም እንዲሁ በተለያዩ አካባቢዎች ጥይት ጥቂት የማይባሉትን ዜጎች ህይወት አጥፍቷል።
በምስራቅ አፍሪቃ የባህር ጠረፍ ላይ ተሰማርቶ የሚገኘዉ የጀርመን የባህር ሃይል፤ የባህር ላይ ወንበዴዎች በአንድ የኢራን መርከብ ላይ የሚያደረሱትን ጥቃት ማከሸፉ ተዘገበ።
የዕለቱን ዝግጅት ለማዳመጥ 16:00 - 17:00 የሚለውን ማገናኛ ይጫኑ። የአንድ ሣምንቱ የስርጭት ኮሮጆም "ዝግጅት"ን በመጫን ሊገኝ ይችላል። የአማርኛ፣ የኪስዋሂሊ፣ የሀውሳ፣የእንግሊዝኛ፣ የፈረንሣይኛ እና የፖርቱጊዝኛ ቋንቋ ሥርጭትን በሚተላለፍበት ጊዜ በኢንተርኔት በቀጥታ ማድመጥም ይቻላል።
በማድመጥ መማር እያዝናና መረጃ የሚሰጥ ዝግጅት ነው።